Tag: ሌሎች ዜናዎች:

Home of best apps

ቻይና ለጠፈር ምርምር የሚውሉ እጅግ ፈጣን አውሮፕላኖች የሚሞከሩበት ዋሻ ገነባች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና ለጠፈር ምርምር የሚውሉ እጅግ ፈጣን የሚባሉ አውሮፕላኖች የሚሞከሩበት ዋሻን መገንባቷ ተገለፀ። ዋሻው 265 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በሰዓት እስከ 30 ሺህ 625 ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘጉ አውሮፕላኖችን የመሞከር አቅም አለው ነው የተባለው። በዋሻው ተፈጥሯዊ የአየር ግፊት እንዲኖር በማድረግ አውሮፕላኑ ሊያጋጥመው በሚችለው የዓየር ሁኔታ ውስጥ እንዲሞከር የሚያስችልም ነው። ባለፈው ወር…
Read more

ፌስቡክ በአሜሪካ የፌዴራል የንግድ ኮሚሽን እየተመረመረ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ50 ሚሊየን ሰዎች የፌስቡክ አድራሻ በአንድ የፖለቲካ አማካሪ ተቋም እንደተበረበረ መገለፁን ተከትሎ የአሜሪካ የንግድ ኮሚሽን በፌስቡክ ላይ ምርመራ እያካሄደ ነው። ምርመራውን የሚያደርገው የአሜሪካ ንግድ ኮሚሽን ለደንቦኞች ጥበቃ የሚያደርግ ገለልተኛ መንግስታዊ ተቋም ነው። ካንብሪጅ አናሊቲካ የተሰኘው ኩባንያ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የ50 ሚሊየን ሰዎችን ግለሰባዊ መረጃዎች በመበርበር ለቅስቀሳ…
Read more

የአለማችን ትንሿ ኮምፒውተር ይፋ ተደረገች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካው አይ ቢ ኤም ቴክኖሎጂ ኩባንያ የተመረተችው የአለማችን ትንሿ ኮምፒውተር ይፋ ተደረገች። እጅግ በጣም ትንሽ እና በየትም ቦታ ለማስቀመጥ ትመቻለች የተባለችው ኮምፒውተር አይ ቢ ኤም ባዘጋጀው ብሄራዊ ጉባኤ ላይ ይፋ ተደርጋለች።  ኮምፒውተሯ በመጠኗ ትንሸ ብትሆንም አስገራሚና ከዚህ በፊት ከነበሩ ኮምፒውተሮች ጋር የመወዳደር አቅም እንዳላት ተነግሯል። ይህቺ ትንሽ ኮምፒውተር በእይታ…
Read more

የፌስቡክ ባለቤት ዙከርበርግ ከመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ይቅርታ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌስቡክ መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎቹ መረጃ ለፖለቲካ ፍጆታ ጥቅም እንዲውል በማድረግ ማህበራዊ ድረ ገፁ ስህተት መስራቱን አመነ። ካንብሪጅ አናሊቲካ የተሰኘው ኩባንያ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የ50 ሚሊየን ሰዎችን የፌስቡክ ግላዊ መረጃዎች በመበርበር ለቅስቀሳ ተጠቅሟል የሚል ክስ ቀርቦበታል። ኩባንያው መተግበሪያዎችን በመጠቀም ከፌስቡክ ላይ መረጃ ሰብስቧል…
Read more

ሩሲያ ሰው የያዘ መንኩራኩር ወደ ዓለም አቀፉ የህዋ ምርምር ማዕከል አመጠቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2010 (ኤፍቢሲ) ሩሲያ ሰው የያዘ መንኩራኩር ካዛኪስታን ከሚገኝ ማዕከል ወደ ዓለም አቀፉ የህዋ ተቋም ማምጠቋን አስታወቀች። መንኩራኩሯ ወደ ህዋ ስትመጥቅ ሦስት ባለሙያዎችን ጭናለች ተብሏል። አንደኛው ከሩሲያው የህዋ ማዕከል ከሮስኮስሞስ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ከአሜሪካው ናሳ መሆናቸው ተገልጿል። በቆይታቸው ወደ 250 የሚደርሱ ሳይንሳዊ ምርምሮችን እንደሚያካሂዱ ተነግሯል። ከእነዚህም መካከል ስነ-ህይወት፣ የስነ-ምድር ሳይንስ፣ በሰው ልጅ…
Read more

የቻይናው ባይዱ ኩባንያ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎችን ለመጀመርያ ጊዜ በጎዳና ላይ መሞከር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ግዙፉ ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ባይዱ፥ ለመጀመርያ ጊዜ አሽከርካሪ አልባዋን ተሽከርካሪ በቤጂን ጎዳናዎች መሞከር ጀምሯል። ሙከራው ባለፈው ሳምነት የዮበር ኩባንያ ውጤት የሆነችው አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪ ጎዳና ላይ የትራፊክ አደጋ በማድረስ የአንድ ሰው ህይወት ካጠፋች ከቀናት በኋላ የተደረገ ነው ተብሏል። በቤጂንግ የአሽከርካሪዎች ህግ መሰረት አሽከርካሪ አልባዋ ተሽከርካሪ ፈቃድ…
Read more

ኒሳን ከ2022 ጀምሮ በየአመቱ 1 ሚሊየን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ሊያቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) መኪና አምራች ኩባንያ ኒሳን ከስድስት ወር በኋላ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን እንደሚያስተዋውቅና በቀጣይ አምስት አመታት የገበያ ሽፋኑን በስድስት እጥፍ ለማሰደግ አቅዶ እየሰራ ነው ተብሏል። የጃፓኑ የተሸከርካሪ አምራች ኩባንያ በፈረንጆቹ 2023 ማብቂያ ላይ 1 ሚሊየን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ከማቅረብ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ባቡሮችንም እንደሚያመርት ገልጿል። ኩባንያው የተለያየ ብቃት ደረጃ…
Read more

የተሽከርካሪዎች ዘመናዊ የፊት መብራቶች በአሽከርካሪዎች እይታ ላይ ተጽህኖ እየፈጠሩ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የምራባዊያኑ የተሽከርካሪ ኢንሹራስ ኩባንያዎች ጥናት እንዳመላከተው 15 በመቶ አሽከርካሪዎች በዘመናዊ የፊት መብራቶች አማካኝነት እይታቸው ላይ ችግር እያደረሰ ነው ብለዋል። ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠሙ የፊት መብራቶች ብርሀን በሌሎች አሽከርካሪዎች እይታ ላይ ለተወሰነ ጊዜ ችግር የሚፈጥርና እይተቻው ወደ ቀድሞው ሁኔታ እስኪመለስ ድረስ በርካታ ሴኮንዶች እንደሚወስድ የኢንሹራስ ኩባንያዎች ያጠኑት ጥናት አመላክቷል። በ2…
Read more

የሰዎችን የአካል እንቅስቃሴ ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል ቀይሮ የሚጠቀመው የስፖርት ማዘውተሪያ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በለንደን ከተማ ቴራ ሀሌ የተባለ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል የደንበኞቹን የአካል እንቅስቃሴ ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል በመቀየርና በመጠቀም የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ ቦጎ አስተዋፅኦ አያበረከተ መሆኑ ተሰምቷል።    ማዕከሉ የደንበኞች የአካል እንቅስቃሴ ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል በመቀየር ሀይል መቆጥብና ማከማቸትም ችሏል ነው የተባለው። የሰበሰበውን ሀይልም ለስፖርት ማዕከሉ ጥቅም ከማዋል ባለፈ በአካባቢው ለሚገኙ የቢዝነስ ተቋማት…
Read more

አፕል እንደ መፅሃፍ የሚታጠፍ ስማርት ስልክ እየሰራ መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግዙፉ የስማርት ስክል አምራች አፕል ፊቱን ወደ ታጣፊ ስማርት ስልኮች ማዞሩ እየተነገረ ነው። ኩባንያው አዲስ እየሰራ ነው የተባለው አይ ፎን ስማርት ስልክ ልክ እንደ መፅሃፍ የሚታጠፍ እና የሚዘረጋ መሆኑንም መረጃዎች ጠቁመዋል። በእሲያ ሀገራት የሚገኙ በርካታ ጥሬ እቃ አቅራቢ ኩባንያዎችም ከአፕል ጋር በመሆን በታጣፊ ስማርት ስልክ ዙሪያ እየሰሩ መሆኑን አረጋግጠዋል…
Read more

ሳዑዲ አረቢያና ሶፍት ባንክ የዓለማችን ግዙፉን የፀሃይ የኃይል ማመንጫ በ200 ቢሊየን ዶላር ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሳኡዲው ልዑል መሃመድ ቢን ሰልማን ሶፍት ባንክና ሳኡዲ አረቢያ በ200 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከፀሃይ ብርሃን የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ (ሶላር) ሊገነቡ መሆኑን አስታወቁ፡፡ በአሜሪካ የሶስት ሳምንት ጉብኝት ላይ የሚገኙት ልዑል ቢን ሰልማን እቅዳቸውን ይፋ ያደረጉት በኒውዮርክ ነው፡፡ ፕሮጀክቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት አብረዋቸው የነበሩት የጃፓኑ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ስራ አስፈጻሚ ማሳዮሺ ሰን…
Read more

ቦይንግ የመረጃ መረብ ጥቃት እንደተቃጣበት አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ የመረጃ መረብ ጥቃት እንደተቃጣበት አስታወቀ። ኩባንያው በተወሰነ የአሰራር ስርዓቱ ላይ እክል የፈጠረ የመረጃ መረብ ጥቃት እንደተፈጸመበት መለየቱን የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ተናግረዋል። ምክትል ፕሬዚዳንቷ ሊንዳ ሚልስ እንዳሉት፥ የተፈጸመው ጥቃት የተወሰነ የአሰራር ስርዓቱ ላይ እክል ከመፍጠር ያለፈ ጉዳት አላደረሰም። በኩባንያው ላይ የተቃጣውን…
Read more