ካስፐርስኪ በአውሮፓ የሚያደርገውን የሳይበር ወንጀል የመከላከል ስራ አቋረጠ

Home of best apps

ካስፐርስኪ በአውሮፓ የሚያደርገውን የሳይበር ወንጀል የመከላከል ስራ አቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ካስፐርስኪ የተባለው የኮምፒውተር ደህንነት ተቋም ከአውሮፓ ተቋማት ጋር በመሆን የሚያከናውነውን የሳይበር ወንጀል መከላከል ስራ ማቋረጡን አስታውቋል።

ኩባንያው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የካስፐርስኪ ሶፍትዌር ተአማኒነት ይጎድለዋል በሚል ያቀረበውን ሞሽን ለመዋቀም መሆኑ ተነግሯል።

ካስፐርስኪ ኩባንያ፥ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ያቀረበበት ውንጀላ ከእውነት የራቀ እና የኩባንያውን ክብር የማይመጥን ነው ብሎታል።

የአውሮፓ ህብረት ውሳኔውን ያሳለፈው አሜሪካ እና ብሪታንያ ካስፐርስኪ ሶፍትዌርን ከተወሰኑ የመንግስት ተቋማት ለማስገድ እርምጃ መውሰዳቸውን ተከትሎ መሆኑም ታውቋል።

የካስፐርስኪ ኩባንያ መስራች ኢዩጂን ካስፐርስኪ በሰጠው መግለጫ፦ በኩባንያው ላይ የቀረበው ውንጀላ ውሸት መሆኑን እና የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ውሳኔ በአውሮፓ ሀገራት የሳይበር ወንጀሎች እንዲስፋፉ የሚያበረታታ ነው ብሏል።

ካስፐርስኪ ኩባንያም ከቀረበበት ውንጀላ ራሱን ነፃ ለማውጣት የራሱን እርምጃ ለመውሰድ አነደሚገደድም አስታውቋል።

ከእርምጃዎቹ ውስጥም ኩባንያው በአውሮፓ ሀገራት የሳይበር በንጀልን ለመከላከል ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ያለውን ስራ ማቋረጥ አዱ መሆኑንም ገልጿል።

ምንጭ፦ www.bbc.com

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *