ሳምሰንግ በፈረንጆቹ 2020 ሙሉ በሙሉ ታዳሽ ሀይል እንደሚጠቀም አስታወቀ

Home of best apps

ሳምሰንግ በፈረንጆቹ 2020 ሙሉ በሙሉ ታዳሽ ሀይል እንደሚጠቀም አስታወቀ

አዲስአበባ፣ሰኔ፣ 7፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ሳምሰንግ በአውሮፓ፣ አሜሪካና ቻይና የሚገኙ ቢሮዎች፣ ማምረቻዎችና ሌሎች መሳሪያዎቹ በቀጣይ ሁለት ዓመታት የታዳሽ ሀይል እንደሚጠቀሙ አስታወቀ፡፡

ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የዲጂታል ከተማ ዋና መስሪያ ቤቱን ወደ ፀሀይ ሀይል መሰብሰቢ በመቀየር ላይ የሚገኝ ሲሆን 42 ሺህ ስኩየር ሜትር የሚረዝም የፀሀይ መሰብሰቢያ ለመግጠም በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የፀሀይ ሀይል መሰብሰቢያው የስድስት ስታድየሞች ስፋት ያለው ነው ተብሏል፡፡

የኩባንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዎን ዮንግ ኪም አለምን መጠበቅ እና የአየር ፀባይ ለውጥን መከላከል ሀላፊነት እንዳለባቸው አስታውቀዋል፡፡

ሳምሰንግ በታዳሽ ሀይል ለመጠቀም የሚያደረገውን ጥረት ከኩባንው ጋር በተለያየ መንገድ የሚሰሩ ተቋማትን በማሳተፍ ስኬታማ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

ከዚህ በፊት አፕል ማሽነሪዎችን፣ ማከፋፈያዎች እና ቢሮዎቹ ሙሉ በሙሉ የታዳሽ ሀይል መጠቀም እንደጀመሩ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡- CNET

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *