የጀርመኑ ኩባንያ ዘመናዊውን ረጅም ተሽከርካሪ በቻይና ለዕይታ አብቅቷል

Home of best apps

የጀርመኑ ኩባንያ ዘመናዊውን ረጅም ተሽከርካሪ በቻይና ለዕይታ አብቅቷል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና እጅግ ዘመናዊው ቅንጡ የመዝናኛና ተሽከርካሪ በትናንትናው እለት ለዕይታ በቅቷል።

ተሽከርካሪው 16 ሜትር ርዝመት ሲኖረው በጀርመናዊው የተሽከርካሪ ዲዛይነር ሉዊጅ ኮላኒ አማካኝነት ዲዛይን የተደረገ ነው ተብሏል።

ተሽከርካሪው ባለጸጎች ለመዝናኛነት የሚጠቀሙበት እጅግ ዘመናዊ ስለመሆኑም ነው የተነገረው።

ይህ ተሽከርካሪ በውስጡ ዘመናዊ የቤት እቃዎችን የያዘ በመሆኑም እንደ ተንቀሳቃሽ መኖሪያ አልያም መቆያ ቤት ሊያገለግልም ይችላል።

sofa.jpg

በአንድ ጊዜ 10 ሰዎችን ማስተናገድ እንዲችል ሆኖ የተሰራ ሲሆን፥ ሰዎቹም በውስጡ የፈለጉትን አይነት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

በውስጡም አየር ማቀዝቀዣ መሳሪያዎች፣ ዘመናዊና ምቹ ሶፋዎችና ወንበሮች፣ ዘመናዊ ዲጅታል ሲኒማ፣ ዘመናዊ ማብሰያ ቤትን አካቷል።

ከዚህ ባለፈም ተጠቃሚዎች ዘመናዊ የመታሻ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ነው የተባለው።

በተጨማሪም ጣራውን በበረንዳ መልኩ እንደ መዝናኛ ሊጠቀሙበትም ይችላሉ።

luxury_recreational_vehicle_1.jpg

ውስጡም እስከ 40 ሜትር ስኩየር ስፋት እንዳለው ነው የተነገረው።

ይህን ዘመናዊ ተሽከርካሪ ለመስራት አምስት አመታት የወሰደ ሲሆን፥ 300 መቶ ባለሙያዎችም ይህን ተሽከርካሪ በመስራት ሂደት ውስጥ ተሳትፈዋል።

ይህን ተሽከርካሪ መግዛት የከጀለ ካለ ደግሞ 2 ነጥብ 9 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መክፈል ይጠበቅበታል።

የጀርመኑ ኩባንያ በቀጣይም 5ኛ ትውልድ ኢንተርኔት ያላቸውንና ፈጣን የዋይ ፋይ ያላቸውን ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ቤቶችን የመስራት እቅድ እንዳለውም አስታውቋል።

ምንጭ፦ ፒፕልስ ደይሊ ቻይና

Goal_4_Web.png

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *