ሻርፕ የተባለው የጃፓን ኩባንያ ቶሽባ ኩባንያን በ36 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሊገዛ መሆኑ ገለጸ

Home of best apps

ሻርፕ የተባለው የጃፓን ኩባንያ ቶሽባ ኩባንያን በ36 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሊገዛ መሆኑ ገለጸ

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 28፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጃፓኑ ሻርፕ ኮርፖሬሽን ቶሽባ ላብቶፕ ኩባንያን በ36 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሊገዛ መሆኑን አስታውቋል።

ሻርፕ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ በላፕ ቶፕ ገበያ የመሳተፍ ፍላጎት ያሳየ ሲሆን፥ ካሳለፍነው የፈረንጆቹ ጥቅምት ወር ጀምሮ ከቶሽባ ላፕቶፕ ኩባንያ የ80ነጥብ1 በመቶ ድርሻ ስምምነት መውስዱ ነው የተገለጸው።

 የቶሽባ የንግድ ምልክት ወደ ሻርብ ኩባንያ ከመቀየሩ በፊትም በታይዋኑ ፎክስኮን ኩባንያ አስተዳደር ስር እንደሚቆይም ታውቋል።

ሻርፕ ኩባንያ ቀደም ሲል ጥራት ያላቸው ቴሌቪዥኖችንና ስማርት ስልኮችን በማቅረብ የሚታወቅ የነበረ ሲሆን፥ ከእስያ የዘርፉ አምራች ኩበንያዎች ጋር ሲወዳደር ከቆየ በኋላ የዛሬ 2 ዓመት በታይዋኑ ፎክስኮን ኩባንያ ስር መካተቱን ዘገባው አስታውሷል።

ሻርፕ ኩባንያ ከፎክስ ኮን ጋር መስራት ከጀመረ በኋላም በቻይና ያለው የቴሌቪዥን ገበያ መነቃቃት ማሳየቱን ዘገባው አመላክቷል።

እስከ ፈረንጆቹ 2015 ቶሽባን ላፕቶፖችን በውል ስምምነት ያሰራው የነበረው የቻይና ኩባንያ የእራሱን ማምረቻ ቻይና ውስጥ ካቆቋመ በኋላ ኩባንያው የቴለቪዥን ንግዱን ለታይላንዱ ሂሴንስ፣ በኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጡ ሸቀጣሸቀጦችን የንግድ ዘርፍ ለቻይና ሚዲያ ግሩፕ ሸጦ ባለፈው ሳምንት የባንክ እዳውን መሸፈኑ ተገልጿል።

ፎክስኮን በዚሁ ቅናሽ የኩባንያው ሽያጭ የተሳተፈ ሲሆን፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የላብቶፕ የገበያ አዋጭነት እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም ሻርፕ ኩባንያ ከፎክስኮን ኩባንያ ጋር በመስራትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰፋፊ የዘርፍን ገበያ የማቅረብ ውል ስምምነት በሚወስዱ ኩባንያዎች በኩል በዝቅተኛ ዋጋ ምርቶችን የማቅረብ ሃሳብ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

 

 

 

ምንጭ፦ reuters.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

_3_ድረገፅ.png

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *