ባራክ ኦባማ ቶክ ሾውና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ከኔትፍሊክስ ጋር ተስማሙ

Home of best apps

ባራክ ኦባማ ቶክ ሾውና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ከኔትፍሊክስ ጋር ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከኔትፍሊክስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቶክ ሾው ለማዘጋጀት ተስማሙ።

የኢንተርኔት መዝናኛ ኩባንያ የሆነው ኔትፍሊክስ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንትና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ ጋር የቴሌቪዥን ቶክ ሾው እና አጫጭርና ዘጋቢ ፊልሞችን ለማዘጋጀት መስማማቱን አስታውቋል።

በስምምነቱ መሰረትም ባራክ ኦባማና ባለቤታቸው ቶክ ሾው፣ አጫጭር ፊልሞች፣ ዘጋቢና ተከታታይ ፊልሞችና ሌሎች የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን የሚያዘጋጁ ይሆናል ተብሏል።

አሁን ላይም የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ለማቀናበር የሚረዳ ኩባንያ አቋቁመዋል።

የመዝናኛን ጨምሮ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችም፥ የኦባማ ሾው የቴሌቪዥን ፕሮግራም አካል ይሆናሉም ነው የተባለው።

አሁን ላይ ለዚህ የሚረዳቸውን ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን፥ በፈረንጆቹ 2019 የመጀመሪያ ወራትም ኦባማ ሾውና የቴሌቪዥን ፕሮግራም ለዕይታ ይበቃል ብሏል ኔትፍሊክስ።

ከቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ቅንብር ባለፈም ኦባማና ባለቤታቸው መድረክ በመምራት፣ በማስተዋወቅ እና የቀጥታ ዝግጅት ፕሮግራሞችን የሚያቀርቡ ይሆናል።

ከስምምነቱ በኋላ ኦባማና ባለቤታቸው የቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻቸውን፥ የጋራ የሆኑ እሴቶችን ማጉላት በሚያስችል መልኩ ለመቃኘት ፍላጎት እንዳላቸውም ተሰምቷል።

ሁለቱ አካላት ከደረሱት ስምምነት ባለፈ ግን የክፍያ መጠን እስካሁን አልተጠቀሰም።

ከዚህ ባለፈም ስምምነቱ ለምን ያክል ጊዜ እንደሚቆይም የተባለ ነገር የለም።

 

 

ምንጭ፦ ሲ ኤን ኤን

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *