የወረቀት ገንዘብ ከገበያ የሚወጣበት ጊዜ እየተቃረበ ይሆን?

Home of best apps

የወረቀት ገንዘብ ከገበያ የሚወጣበት ጊዜ እየተቃረበ ይሆን?

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቅርብ ዓመታት ውስጥ የወረቀት ገንዘብ በኤሌክትሮኒክስ ንግድ፣ በሞባይል ክፍያና በካርድ ሊተካ እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ማንችስተር ከተማና በቴኔስ የተደረጉ የሙዚቃ ድግሶች ሙሉ ለሙሉ ከጥሬ ገንዘብ ውጪ መከናወናቸውን እንደምሳሌ በማንሳት የኤሌክትሮኒክስ ግብይት በቅርብ ዓመታት ግብይቱን ሊቆጣጠረው ይችላል ይላሉ፡፡

በተለያዩ ሀገራት በገበያ ስፍራዎች የኤሌክትሮኒክስ ካርድ የሚያነቡ ትንንሽ ማሽኖች ማየትም እየተለመደ መጥቷል፡፡

አንድ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ግለሰብ ጥሬ ገንዘብ ከያዙ ሦስት ዓመት እንዳስቆጠሩ ገልጸው፥ ለድንገተኛ ጊዜ መያዝ ያለባቸውን ገንዘብ በኪሳቸው ማስቀመጥ መተዋቸውን ተናግረዋል፡፡

በዓለም ላይ የሚደረጉ የኤሌክትሮኒክስ ግብይቶች በየዓመቱ በ11 በመቶ እያደጉ እንደሆነ ጥናቶች አመላክተዋል፡፡
በአንጻሩ አሜሪካውያን ከሞባይል ክፍያ ጋር በተያያዘ ያላቸው ልምድ እጅግ አናሳ ነው ተብሏል፡፡

ከአውሮፓ ሀገራት መካከል ኖርዌይና ስዊዲን እንዲሁም ከአፍሪካ ናይጄሪያ ከወረቀት ገንዘብ የህትመት ውድነት ጋር በተያያዘ ሀገራቱ ጥሬ ገንዘብን ከገበያ ለማውጣት አቅደው በመስራት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

እንዲሁም የፎሬክስ ቦነስ ጥናት እንደሚያሳየው ጥሬ ገንዘብ አልባ ከተባሉት ሀገራት መካከል ካናዳ ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች፡፡

ሁለተኛዋ ሀገር ስዊድን ስትሆን 20 በመቶ የሚደርስ ግብይቷን ብቻ ነው በጥሬ ገንዘብ የምትገበያየው ተብሏል፡፡

አዲስ የመጡት የቴክኖሎጂ ውጤቶች የወረቀት ገንዘብን ያስቀራሉ ቢባልም፤ ዛሬም ቢሆን 85 በመቶ በዓለም ላይ የሚከናወኑት ግብይቶች በጥሬ ገንዘብ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

አንድ አሜሪካዊ ባለሙያ አንዳንዶች ላለፉት 20 ዓመታት የጥሬ ገንዘብን መጨረሻ ቢተነብዩም እስከአሁን ድረስ መኖሩን ጠቅሰው፥ ምናልባትም ከገበያ ሊወጣ የሚችለው ከረጅም ዓመታት በኋላ ነው ብለዋል፡፡

 

ምንጭ፦ ሲኔት
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *