በራሱ ጊዜ ወደ መኪናነት መቀየር የሚችል ሮቦት ተዘጋጀ

Home of best apps

በራሱ ጊዜ ወደ መኪናነት መቀየር የሚችል ሮቦት ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጃፓን ኢንጅነሮች ሰው መያዝ ሚችልና ወደ መኪናነት መቀየር የሚችል ሮሆቦት ማዘጋጀታቸውን ይፋ አደረጉ፡፡

በሮቦት የቴክኖሎጅ ፈጠራ ታሪክ የመጀመሪያው አስደናቂ ክስተት አንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

ሁለት ሰዎችን የሚይዘው እና በደቂቃ ውስጥ ወደ ስፖርት መኪናነት የሚቀየረው ይህ ሮቦት 3 ነጥብ 7 ሜትር እንደሚረዝም ተነገሯል፡፡

ሮቦቱን ለማዘጋጀት የህፃናት አንሜሽን ፌልም መነሻ እንደሆናቸው አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

ወደ መኪናነት መቀየር የሚችለው ሮቦት ሰዎችን ለማነሳሳት እና የማሰብ አቅምን ለማስፋት የሚያስችል ሲሆን ውድ የሚባል መጫዎቻ የሚያወጣውን ዋጋ ያወጣል ተብሏል፡፡

በቀጣይም ይህን ቴክኖሎጅ በመናፈሻ ፓርኮች መጫዎቻነት አና ለጎዳና ትርኢቶች አገልግሎት መስጠት በሚችልበት ሁኔታ እንደሚዘጋጅ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡- ቴሌግራም

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *