አንጎላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደህዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት ስራ አቆመች

Home of best apps

አንጎላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደህዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት ስራ አቆመች

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጎላ በሩሲያ እርዳታ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ህዋ ያመጠቀቻት ሳተላይት ስራ ማቆን አስታወቀች።

አንጎሳት 1 በመባል የጠራው ሳተላይት ከካዛኪስታን ጣቢያ ወደ ህዋ የተላከችው ከአራት ወራት በፊት ነበር።

300 ሜትር ያህል የምትረዝመው ይህ ሳተላይት ወደ ህዋ የተላከችው ለመገናኛ አገልግሎት ለማዋል እንደነበር ተገልጿል።

ሳታላይቷ የቴክኒክ እክል የገጠማት ከመጠቀች ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ሲሆን፥ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም ግንኙነቷ መቋረጡን ነው ሩሲያ የገለጸችው።

ሩሲያ ለአንጎላ በገባችው ዋስትና መሰረት ያለምንም ወጪ በ2020 ምትክ ሳተላይት እንደምትገነባላት አስታውቃለች።

ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ሳተላይታቸውን ወደህዋ ያመጠቁ አገራት ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ጋና ሲሆኑ፥ የተላኩትም ለመገናኛ ዘዴ፣ ለትምህርት እና ለወታደራዊ አገልግሎት እንዲውሉ ታስቦ እንደሆነ ይታወሳል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *