በቻይና የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ አውቶቡስ ለእይታ ቀርቧል

Home of best apps

በቻይና የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ አውቶቡስ ለእይታ ቀርቧል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 16 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ለእይታ ቀርቧል።

አውቶቡሱ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፥ ፉጂያን ግዛት መዲና በሆነችው ፉዡ ከተማ በተዘጋጀ አውደ ርዕይ ላይ ነው ለእይታ የቀረበው።

ዛሬ በሚጠናቀቀው አውደ ርዕይ ላይ በሚኖረው ቆይታም አውቶቡሱ እስከ 1 ሺህ የሚደርሱ መንገደኞችን ያጓጉዛል ተብሎ ይጠበቃል።

driverless_bus_1.jpg

አውቶቡሱ አውደ ርዕዩ ከተጠናቀቀ በኋላም መደበኛ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

መደበኛ አገልግሎት ይጀምራል የተባለው አውቶቡስ ምን ያክል ሰዎች እንደሚጭንና የትራንስፖርት ዋጋውን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።

driverless_bus_2.jpg

አሁን አሁን የከተማ ትራንስፖርት ብቻ የሚሰጡ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎች በብዛት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛል።

ኡበር ኩባንያ በዚህ ዘርፍ ቀዳሚው ሲሆን፥ ይህን አገልግሎቱን በተለያዩ ሃገራት ሲሞክር ቆይቷል።

ኒሳንም ይህን አገልግሎት በጃፓን ለመጀመር ሂደት ላይ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

ባለፈው መጋቢት ወር ኡበር በአሪዞና ግዛት አንድ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪው የሰው ህይዎት ማጥፋቱን ተከትሎ በግዛቲቱ የሚያደርገውን ሙከራ ማቋረጡ የሚታወስ ነው።

 

 

 

ምንጭ፦ ፒፕልስ ደይሊ ቻይና

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *