ማይክሮ ሶፍት ኩባንያ የምርጫ ሂደትን ከመረጃ መንታፊዎች የሚታደግ ቴክኖሎጂውን ይፋ አደረገ

Home of best apps

ማይክሮ ሶፍት ኩባንያ የምርጫ ሂደትን ከመረጃ መንታፊዎች የሚታደግ ቴክኖሎጂውን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ሚያዚያ 8፣ 2010፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የበይነ መርብ መስፋፋት መረጃዎችን ከምንግዜውም የበለጠ ለመረጃ መንታፊዎች ተጋላጭ ያደረጋቸው ሲሆን፥ ሰዎቹ የምርጫ ሂደትን የመሰሉ መሰረታዊ ጉዳዮችን ከእነዚህ የመረጃ መንታፊዎቹ የመጠበቅ ጉዳይ አሳሳቢ አድርጎታል። 

በ2016 የአሜሪካ የምርጫ ሂደት ላይ ሩሲያ ተጫወተችው የተባለው ሚናም በአብዛኛዎቹ ዘንድ የሚታወስ ነው።

 በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነው የማይክሮ ሶፍት ኩባንያ የአሜሪካን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የዴምክራሲ ተከታይ ሀገራት የምርጫ ሂደትን ከመረጃ 

መንታፊዎች ለመጠበቅ የሚያስችለውን የዴሞክራሲ ፕሮግራም መከላከያ ቴክኖሎጂ በማስተዋወቅ አዲስ ብስራት ይዞ እንደመጣ እየተገለጸ ነው ።

በዚህም ኩባንያው ከተለያዩ ሀገራት መንግስታትና ከሌሎች ኩባንያዎች ጋር በመሆን ምርጫን ከመረጃ በርባሪዎቹ በመከላከል፣ በበይነ መረብ የሚስተናገዱ የፖለቲካ ማስታወቂያዎችን ግልጽ በማድረግ፣ የምርጫ መረጃዎች እንዳይበረበሩ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት እና የሳይበር ጥቃቶችን ለመጠቆም የሚያስችሉ ስራዎችን እንደሚሰራ አስታውቋል ተብሏል።

የምርጫ ሂደቶችና የፖለቲካ መረጃዎችን ለማስተላለፍ የሚዘረጉ የመሰረተ ልማት አውታሮች የሳይበር ጥቃት ዒላማዎች እንደሆኑ ኩባንያው በብሎጉ ዘግቧል ተብሏል።

በፈረንጆቹ ህዳር ወር 2018 በአሜሪካ ለሚደረገው የመካከለኛ ጊዜ ምርጫና ለ2020 የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ኩባንያው አዲሱ ስራውን ተግባራዊ ያደርጋል ተብሏል።

በዚሁ ዓመትም ኩባንያው ቴክኖሎጂውን ወደ ሌሎች አገራት የማስፋፋት ሙከራ እንደሚያደርግም ተገልጿል።

 

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ fossbytes.com

 

ተተርጉሞ የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *