ሩሲያ ቴሌግራም የተባለውን የማህበራዊ ትስስር ገፅ አገደች

Home of best apps

ሩሲያ ቴሌግራም የተባለውን የማህበራዊ ትስስር ገፅ አገደች

አዲስአበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2010 (ኤፍቢሲ) የሩሲያ መንግስት የማህብራዊ ትስስር ገፅ የሆነውን ቴሌግራም አገልግሎትን በሀገሪቱ አገደ።

የሀገሪቱ የሚዲያ ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት ቴሌግራም የተጠቃሚዎቹን የመረጃ ቋት የሚያስቀምጥበትን የይለፍ መስመር አልሰጥም በማለቱ መታገዱ ነው የተገለፀው።

ቴሌግራም ቀነ ገደቡ መጋቢት መጨረሻ ላይ እንደነበረ ተገልጿል።

ኩባንያው የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች መረጃን አሳልፎ የሚሰጥበት መመሪያ የለኝም ብሏል።

የሀገሪቱ የደህንነት ኃላፊዎች የይለፍ መረጃውን የፈለጉት ወደፊት በሃገሪቱ ሊከሰት የሚችለውን የሽብር አደጋ ለመከላከል መሆኑን አብራርተዋል።

የቴሌግራም የህግ አማካሪ ፓቬል ቺኮቭ እግዱን መሰረተ ቢስ ብለውታል።

እንዲሁም የግለሰቦችን የግል ንግግር ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ኢህገመንግስታዊ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ወቅት በብዛት በሩሲያና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን፥ 200 ሚሊየን የሚደርሱ ንቁ ተጠቃሚዎች እንዳሉት አስታውቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጠቃሚዎቹ ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፤ ከነዚህም ምክንያቶች አንዱ የተባለው በተለየ መልኩ ያለው የደህንነት አያያዝ መሆኑ ነው የተገለፀው።

 

 

ምንጭ፦ቢቢሲ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *