በአውሮፓ የአሜሪካ የዜና ድረ ገጾች ተደራሽ እየሆኑ አይደለም ተባለ

Home of best apps

በአውሮፓ የአሜሪካ የዜና ድረ ገጾች ተደራሽ እየሆኑ አይደለም ተባለ

አዲስ አባባ፣ ሰኔ 19፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአውሮፓ የተወሰኑ የአሜሪካ የዜና ድረ ገጾች ተደራሽ እየሆኑ እንዳልሆነ ተገልጿል።

የአሜሪካ ታዋቂ የሆኑት ሎስአንጀለስ ታይምስ ና ኒውዮርክ ዲያሊ ኒውስን ጨምሮ የተለያዩ የዜና ድረ ገጾች በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ተደራሲያን ዘንድ ተደራሽ እየሆኑ እንዳልሆነ ነው የተገለጸው።

በድረ ገጹ ላይ እገዳው የተጣለው በአውሮፓ ህብራት አባል ሀገራት ላይ አዲሱ የመረጃ ጥበቃ ህግ ተግበራዊ መደረግ ከጀመረበት ከወር በኋላ መሆኑም ታውቋል።

ችካጎ ትሪቡን፣ ዘ ኦርላንዶ፣ ሰንቲኔና ባልቲሞር ሰን እገዳው ከተጣለባቸው የአሜሪካ የዜና ድረ ገጾች መካከል እንደሚገኙበትም ተመላክቷል።

አዲሱ የመረጃ ጥበቃ ህግ የህብረቱ አባል ሀገራት ዜጎችን የመረጃ ባለቤትነት መብት ለማስከበር የወጣ መሆኑን ዘገባው ያመላክታል።

በህብረቱ አባል ሀገራት ድረ ገጽ ዜና አገልግሎትየሚሰጡ ኩባንያዎች ህጋዊ መሰረትና ተጠያቂነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተገልጿል።

በአዲሱ የደንበኞች መረጃ ጥበቃ ህግ ኩባንዎች የደንበኞችን መረጃ ለመጠቀም የሚያስችሉ 6 ህጋዊ መሰረት ስምምነቶች መቀመጡም ተጠቁሟል።

በአውሮፓ መረጃ ላይ የሚሰሩ ኩባንያዎችም የግለሰቦቸን መረጃ የመጠቀም ፍላጎታቸውንና ለምን አላማ መረጃዎችን እንደሚጠቀሙ ለደንበኞች በማስረዳት ፈቃድ ማግኘት ያለባቸው መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

በዚህም አዲሱ የደንበኞች መረጃ ህግ በአውሮፓ አባል ሀገራት ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ በኋላ ዋሽንግተን ፖስትና ታይምስ በአዲሱ ህግ መሰረት ስምምነት መፈራረም የሚጠበቅባቸው በመመሆኑ እገዳ የተደረገባቸው መሆኑ ታውቋል።

የደንበኞች መረጃ ጥበቃ ህጉ በሳለፍነው ግንቦት 25 ተግባራወዊ መደረጉን ዘገባው አስቷውሷል።

 

 

 

ምንጭ፦ bbc.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *