የደም ምርመራና ትንተና መረጃዎችን ለመስራት የሚያስችል ሮቦት መስራታቸውን ተመራማሪዎቹ ገለጹ

Home of best apps

የደም ምርመራና ትንተና መረጃዎችን ለመስራት የሚያስችል ሮቦት መስራታቸውን ተመራማሪዎቹ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደም ምርመራና መረጃዎቸን ትንተና ለመስራት የሚያስችል ሮቦት መስራታቸውን ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።

በሩትገርስ ዩንቨርስቲ ተመራማሪዎች የተሰራው አዲሱ ሮቦት ትክክለኛና ወቅታዊ የደም ምርመራ ውጤትና ትንተና መረጃ በመስጠት የዘርፉን ባለሙያዎችና ህሙማን ያግዛል ተብሏል።

ቴክኖሎጂው በተገጠመለት ካሜራ የሰዎቹን እጅ ስካን በማድረግ በቀላሉ የደም ስሮችን በመለየት ቀደም ሲል ባለሙያዎች በመርፌ በመሰርሰር የደም ስሮችን ይፈልጉ የነበረውን አሰራር ያስቀራል ነው የተባለው።

መሳሪያው የደም ምርመራና ትንተና ስሌቱን የሚሰራው ከሰዎች ንክኪ ውጭ መሆኑም ታውቋል።

የደም ስሮችን ከለየ በኋላም ከውሃማው የደም ክፍል የደም መረጃዎቸን በመለየት ትንተና ለመስራት እንደሚችል የተገለጸ ሲሆን፥ ውጤቱንም ‘‘ማክሮ ፍሉድ አሬይ’’ በተባሉ የቴክኖሎጂው ክፍል እንደሚያሳውቅ ነው የተገለጸው።

ቴክኖሎጂው አሁን ላይ በሰዎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃድ ያልተሰጠ ሲሆን ፥ ተመራማሪዎቹ ለዚሁ ተግባር ባዘጋጁት ሰው ሰራሽ እጅ ላይ መሞከራቸው ታውቋል። 

‘‘ማይክሮቤድስ’’ በተባሉ መሳሪያዎች አማካኝነት በሰው ሰራሽ እጁ ላይ በደም ዑደት ተመሳስለው በተሰሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ በዚሁ ሮቦት የተደረገው ሙከራ ውጤታማ መሆኑ ተመላክቷል።

ምንጭ፦ extremetech.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *