ሞዚላ በድምፅ ትእዛዝ የሚሰራ የድረ ገጽ ብራውዘር እየሰራ ነው

Home of best apps

ሞዚላ በድምፅ ትእዛዝ የሚሰራ የድረ ገጽ ብራውዘር እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሞዚላ በድምፅ ትእዛዝ የሚሰራ የድረ ገጽ መክፈቻ (ብራውዘር) እየሰራ መሆኑ ተነግሯል።

አዲሱ የሞዚላ ብራውዘር ፕሮጀክት “ስኮውት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፥ ያለ ምንም የእጅ ንክኪ ተጠቃሚዎች በድምፅ የሚያዙትን ነገሮች ብቻ የሚከፍት ነው ተብሏል።

የሞዚላ የድምፅ ብራውዘር ድረ ገፆችን ከመክፈት በዘለለም በድምፅ ትእዛዝ ወደ ላይ እና ወዳ ታች በማድረግ ለማንበብ የሚያችለን መሆኑም ተነግሯል።

“ስኮውት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሞዚላ የድምፅ ብራውዘር በአካል ጉዳት ምንክያት እጃቸውን እንደ ልብ ለማንቀሳቀስ ለሚቸገሩ እና የእይታ ጥራት እግር ላለባቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው ተብሏል።

እንዲሁም ሞዚላ በድረ ገጽ መክፈቻ (ብራውዘር) ኢንደስትሪ ውስጥ ዳግም እንዲያንሰራራ የሚረዳው እንደሆነም በብዛት እየተነገረ ነው።

በአሁኑ ወቅት በድረ ገፅ መክፈቻ (ብራውዘር) ገበያው ውስጥ ሞዚላ የነበረው ድርሻ በአብዛኛው በጎግል ክሮም የተቀማ ሲሆን፥ ይህን ድርሻውን ለማስመለስ የሚረዳው ፈጠራ መሆኑም ተነግሯል።

በድምፅ በሚታዘዘው ብራውዘር ዙሪያ ዝርዝር የሆኑ መረጃዎች እስካሁን አለመውጣታቸውም ተነግሯል።

ምንጭ፦ fossbytes.com

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *