Tag: ሌሎች ዜናዎች:

Home of best apps

ህንድ ፌስ ቡክን ጨምሮ መልዕክት መላላኪያ ማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲዘጉላት ጠየቀች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድ የቴሌኮም ዘርፍ ባለሙያዎቿ የተወሰኑ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾችና መተግበሪያዎችን እንዲያግዱላት እየጠየቀች ነው። የህንድ መንግስት የሃገሪቱ የቴሌኮም ዘርፍ ባለሙያዎች ፌስ ቡክ እና በኩባንያው የሚተዳደሩትን ዋትስ አፕን እና ኢንስታግራምን ማገድና አገልግሎት እንዳይሰጡ ማቋረጥ የሚችሉበትን መንገድ ይፈልጉ ዘንድ ጠይቋል ነው የተባለው። ሬውተርስ ጉዳዩን በተመለከተ የሚገልጽ መረጃ አገኘሁ…
Read more

ፌስቡክ በብሪታንያ የመረጃ ቁጥጥር ማእከል የ500 ሺህ ፓውንድ ቅጣት ተጣለበት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሪታንያ የመረጃ ቁጥጥር ማእከል በፌስቡክ ላይ የ500 ሺህ ፓውንድ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ ማሳለፉ ተነግሯል። ማእከሉ በፌስቡክ ላይ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው ኩባንያው የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃ መጠበቅ ላይ ክፍተት አሳይቷል በሚል ነው። የኢንፎርሜሽን ኮሚሽነር ቢሮ እንዳስታወቀው፥ ፌስቡክ ካንብሪጅ አናላቲካ የሚባለው ድርጅት የተደንበኞቹን መረጃ እንዲወድስ አድርጓል፤ አሁን ደግሞ ኩባንያው መረጃውን ማጥፋቱን…
Read more

ሞዚላ በድምፅ ትእዛዝ የሚሰራ የድረ ገጽ ብራውዘር እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሞዚላ በድምፅ ትእዛዝ የሚሰራ የድረ ገጽ መክፈቻ (ብራውዘር) እየሰራ መሆኑ ተነግሯል። አዲሱ የሞዚላ ብራውዘር ፕሮጀክት “ስኮውት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፥ ያለ ምንም የእጅ ንክኪ ተጠቃሚዎች በድምፅ የሚያዙትን ነገሮች ብቻ የሚከፍት ነው ተብሏል። የሞዚላ የድምፅ ብራውዘር ድረ ገፆችን ከመክፈት በዘለለም በድምፅ ትእዛዝ ወደ ላይ እና ወዳ ታች በማድረግ ለማንበብ የሚያችለን…
Read more

በአውሮፓ የአሜሪካ የዜና ምንጮች በአህጉሪቷ ድረገጾች ላይ እንዳይታዩ ታገዱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት የመረጃ ከለላ ህግን በስራ ላይ በማዋሉ ምክንያት ታዋቂነትን ያተረፉ የአሜሪካ የዜና ምንጮች በአህጉሪቷ ድረገጾች እንዳይታዩ ታገዱ፡፡ በአውሮፓ በሚገኙ ሀገራት ከታገዱት የዜና ምንጮች መካከል ቺካጎ ታይምስና ሎስአንጀለስ ታይምስ ይገኙበታል ተብሏል፡፡ አጠቃላይ የመረጃ ከለላ መመሪያ በሚል የወጣው ህግ ለአውሮፓውያን ዜጎች በመረጃ አጠቃቀም ዙሪያ ተጨማሪ መብት ያጎናጽፋል ተብሏል፡፡ አሁን የወጣው…
Read more

ቲዊተር 330 ሚሊየን ደንበኞቹ የይለፍ ቁልፎቻቸውን እንዲቀየሩ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ፣26፣(ኤፍ.ቢ.ሲ) ቲዊተር 330 ሚሊየን ደንበኖቹ የይለፍ ቁልፎቻቸውን መቀየር እንዳለባቸው ያስጠነቀቀው የውስጥ አሰራሮቹ ላይ ችግሮች እንደገጠሙት ካረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል። የማህበራዊ ድረገጹ የደንበኞቹ የይለፍ ቁልፎች በሌሎች ሰዎች አገልግሎት ላይ ይዋሉ አይዋሉ ለማረጋገጥ እንዳልቻለም ነው የተገለጸው።   ኩባንያው ከጥቂት ሳምንታት በፊት ችግሩ እንደተከሰተ ያረጋገጠ ሲሆን፥ የተከሰቱ ጉድለቶችን እንዲያርሙ ለኩባንያው ሰራተኞች ሪፖርት ማድረጉም ታውቋል።  በዚህም ደንበኞቹ የይለፍ…
Read more

ዩ ቲዩብ፣ ፌስ ቡክ እና አፕል የአሌክስ ጆንስን የሴራ ንድፈ ሃሳብ ስራዎች ከገጻቸው አገዱ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶስት የማህበራዊ ትስስር ገጾች አወዛጋቢው የሴራ ንድፈ ሃሳብ አዘጋጅና አቅራቢ አሌክስ ጆንስ ስራዎች ላይ እገዳ ጥለዋል። ፌስ ቡክ፣ ዩ ቲዩብ እና አፕል ግሰለቡ በቶክ ሾው ፕሮግራሞቹ በማዘጋጀት በገጾቹ ላይ የሚለጥፋቸውን ተንቀሳቃሽ ምስሎች ማገዳቸውን አስታውቀዋል። ለዚህ ደግሞ አሌክስ ጆንስ የሚያነሳቸው ሃሳቦች እጅግ አወዛጋቢና የኩባንያዎቹን የማህበራዊ ሚዲያ…
Read more

ተስላ ኩባንያ በዓመት 500 ሺህ ተሽከርካሪዎቸን ማምረት የሚችል ፋብሪካ በሻንጋይ ሊከፍት ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ03፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተስላ የተባለው ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ በዓመት 500 ሺህ ተሽከርካሪዎቸን ማምረት የሚችል ፋብሪካ በቻይናዋ ከተማ ሻንጋይ ሊከፍት ነው ተብላል። ኩባንያው ከሻንጋይ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ሊንጋንግ በተባለው አካባቢ የተሽከርካሪ ፋብሪካውን ለመገንባት መፈራረሙም ታውቋል። ኩባንያው በቻይና ፋብሪካውን ለመክፈት ያቀደው በኤለክትረክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በቻይና ሰፊ ገበያ እንዳላቸው በማረጋገጥና አሁን ላይ አሜሪካ ወደ ቻይና የሚገቡ…
Read more

ካስፐርስኪ በአውሮፓ የሚያደርገውን የሳይበር ወንጀል የመከላከል ስራ አቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ካስፐርስኪ የተባለው የኮምፒውተር ደህንነት ተቋም ከአውሮፓ ተቋማት ጋር በመሆን የሚያከናውነውን የሳይበር ወንጀል መከላከል ስራ ማቋረጡን አስታውቋል። ኩባንያው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የካስፐርስኪ ሶፍትዌር ተአማኒነት ይጎድለዋል በሚል ያቀረበውን ሞሽን ለመዋቀም መሆኑ ተነግሯል። ካስፐርስኪ ኩባንያ፥ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ያቀረበበት ውንጀላ ከእውነት የራቀ እና የኩባንያውን ክብር የማይመጥን ነው ብሎታል።…
Read more

ፌስ ቡክ ከመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ለደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንደማይፈጽም ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት17፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስ ቡክ ካምብሪጅ አናሊይቲካ በደንበኞቹ ላይ አደረሰ ከተባለው የመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ የካሳ ክፍያ እንደማይከፍል አስታውቋል። ኩባንያው ለደንበኞቹ የካሳ ክፍያ የማይፈጽም መሆኑን የገለጸው ከዚህ ሳምንት በፊት በብራሰልስ የአውሮፓ ህብረት ህግ አውጪዎች ለኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ማርክ ዙከርበርግ የክፍያ ከሳን በተመለከተ ላቀረቡላቸው ጥያቄ በተሰጠ የጽሁ ምላሽ ነው ተብሏል። የአውሮፓ ህብረት ህግ አውጪዎች የህብረቱ ሀገራት…
Read more

ተመራማሪዎች ያለገደብ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል አዲስ ፕላስቲክ ሰሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተመራማሪዎች ቡድን በአይነቱ አዲስ የሆነ ፕላስቲክ መስራታቸው ተነግሯል። የኮለራዶ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የሰሩት አዲሱ ፕላስቲክ በመልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ዘዴ ያለ ገደብ በድግግሞሽ በማምረት ለመጠቀም የሚያስችል ነው። በዩኒቨርሲቲው የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ፕሮፌሰር ኢዩጂን ቼን እንደሚናገሩት፥ አዲሱ ግኝት በየዓመቱ የምንጥለውን የፕላስቲክ ቆሻሻ መጠን ለመቀነስ አይነተኛ መፍትሄ ነው ብለዋል። በየዓመቱ 12…
Read more