Tag: ሌሎች ዜናዎች:

Home of best apps

የቻይናው ዜድቲኢ በአሜሪካ የተጣለበትን የ1 ቢሊየን ዶላር ቅጣት ሊከፍል ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይናው ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ የሆነው ዜድቲኢ በዩናይትድ ስቴትስ የተጣለበትን የአንድ ቢሊየን ዶላር ቅጣት ለመክፈል ከሀገሪቱ ጋር መስማማቱ ተገለጸ፡፡ ኩባንያው ላይ ቅጣቱ ሊጣል የቻለው ሀገሪቷ ማዕቀብ ከጣለችባቸው ከኢራንና ሰሜንኮሪያ ጋር የንግድ ልውውጥ አድርጓል በሚል መሆኑ ተነግሯል፡፡ ኩባንያው ወደ ገበያ ከመግባቱ በፊት እንደ ማስያዣ ወይንም መንግስት ያስቀመጣቸው ቅድመሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ እንዲሁም…
Read more

ማይክሮሶፍት የመረጃ ማእከሉን ውቅያኖስ ውስጥ አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመረጃ (ዳታ) ማእከላት ለዓለማችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ወሳኝ እየሆኑ ከመጡ ዋል አደር ብለዋል። የዳታ ማእከላት ከሌሉ የድረ ገፅ አገልግሎቶች፣ መረጃዎቻችንን ለመጠባበቂያነት የምናከማችባቸው እንደ ክላውድ ያሉ የመረጃ ማስቀመጫ ቋቶች አይኖሩም ነበር። ታዲያ እነዚህ የመረጃ ማከማቻ ማእከላት ስራቸውን ለመስራት እና ራሳቸውን ለማቀዝቀዝ ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ሀይል እንደሚጠቀሙም ይታወቃል።ይህ ደግሞ ለአካባቢ ብክለት…
Read more

ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ከአየር ውስጥ የሚሰበስበው ቴክኖሎጂ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የካናዳ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ለጤናችን ጎጂ የሆኑ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ከአካባቢያችን አየር ውስጥ በቀላሉ የሚሰበስብ መሳሪያ መስራቱን አስታውቋል። ካርቦን ኢንጂነሪንግ የተባለው እና እንደ ቢል ጌትስ ካሉ ባለሀብቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው ኩባንያው፥ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ ከአካባቢ አየር ውስጥ እንዴት መሰብሰብ ይቻላል የሚለው ላይ ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም በአየር…
Read more

የጀርመኑ ኩባንያ ዘመናዊውን ረጅም ተሽከርካሪ በቻይና ለዕይታ አብቅቷል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና እጅግ ዘመናዊው ቅንጡ የመዝናኛና ተሽከርካሪ በትናንትናው እለት ለዕይታ በቅቷል። ተሽከርካሪው 16 ሜትር ርዝመት ሲኖረው በጀርመናዊው የተሽከርካሪ ዲዛይነር ሉዊጅ ኮላኒ አማካኝነት ዲዛይን የተደረገ ነው ተብሏል። ተሽከርካሪው ባለጸጎች ለመዝናኛነት የሚጠቀሙበት እጅግ ዘመናዊ ስለመሆኑም ነው የተነገረው። ይህ ተሽከርካሪ በውስጡ ዘመናዊ የቤት እቃዎችን የያዘ በመሆኑም እንደ ተንቀሳቃሽ መኖሪያ…
Read more

አሜሪካ የዓለም ፈጣኑንና ትልቁን ኮምፒተር ይፋ አድርጋለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ የዓለም ፈጣኑንና ትልቁን ኮምፒተር ይፋ ማድረጓ ተገልጿል። በዘርፉ በቻይና ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በማሻሻል የዓለም ፈጣኑንና ትልቁን ኮንፒተር አገልግሎት ላይ ማዋሉን የአሜሪካው ዓለም አቀፍ የማሽን ንግድ ኮርፖረሽን ባሳለፍነው አርብ ይፋ ማድረጉ ተገልጿል።  ሳሚት የሚል ስያሜ የተሰጠው ይኼው ፈጣኑና ትልቁ ኮምፒዩተር አሁን ላይ አሜሪካ ተንሴ ውስጥ ኦካክ ሪጅ ብሄራዊ ቤተሙከራ…
Read more

ሳምሰንግ በፈረንጆቹ 2020 ሙሉ በሙሉ ታዳሽ ሀይል እንደሚጠቀም አስታወቀ

አዲስአበባ፣ሰኔ፣ 7፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ሳምሰንግ በአውሮፓ፣ አሜሪካና ቻይና የሚገኙ ቢሮዎች፣ ማምረቻዎችና ሌሎች መሳሪያዎቹ በቀጣይ ሁለት ዓመታት የታዳሽ ሀይል እንደሚጠቀሙ አስታወቀ፡፡ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የዲጂታል ከተማ ዋና መስሪያ ቤቱን ወደ ፀሀይ ሀይል መሰብሰቢ በመቀየር ላይ የሚገኝ ሲሆን 42 ሺህ ስኩየር ሜትር የሚረዝም የፀሀይ መሰብሰቢያ ለመግጠም በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የፀሀይ ሀይል መሰብሰቢያው የስድስት ስታድየሞች ስፋት ያለው ነው…
Read more

ካስፐርስኪ በአውሮፓ የሚያደርገውን የሳይበር ወንጀል የመከላከል ስራ አቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ካስፐርስኪ የተባለው የኮምፒውተር ደህንነት ተቋም ከአውሮፓ ተቋማት ጋር በመሆን የሚያከናውነውን የሳይበር ወንጀል መከላከል ስራ ማቋረጡን አስታውቋል። ኩባንያው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የካስፐርስኪ ሶፍትዌር ተአማኒነት ይጎድለዋል በሚል ያቀረበውን ሞሽን ለመዋቀም መሆኑ ተነግሯል። ካስፐርስኪ ኩባንያ፥ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ያቀረበበት ውንጀላ ከእውነት የራቀ እና የኩባንያውን ክብር የማይመጥን ነው ብሎታል።…
Read more

ሞዚላ በድምፅ ትእዛዝ የሚሰራ የድረ ገጽ ብራውዘር እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሞዚላ በድምፅ ትእዛዝ የሚሰራ የድረ ገጽ መክፈቻ (ብራውዘር) እየሰራ መሆኑ ተነግሯል። አዲሱ የሞዚላ ብራውዘር ፕሮጀክት “ስኮውት” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፥ ያለ ምንም የእጅ ንክኪ ተጠቃሚዎች በድምፅ የሚያዙትን ነገሮች ብቻ የሚከፍት ነው ተብሏል። የሞዚላ የድምፅ ብራውዘር ድረ ገፆችን ከመክፈት በዘለለም በድምፅ ትእዛዝ ወደ ላይ እና ወዳ ታች በማድረግ ለማንበብ የሚያችለን…
Read more

የአውስትራሊያ ፍርድ ቤት በአፕል ኩባንያ ላይ የ6 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ቅጣት ወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የቴክኖሎጅ ኩባንያ አፕል በአውስትራሊያ ፍርድ ቤት የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል። ኩባንያው 6 ነጥብ 7 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ ቅጣት ነው የተላለፈበት። የኩባንያው ደንበኞች በገዙት አይ ፎን ስልክና አይ ፓድ ላይ ለደረሰው ጉዳት የዋስትና ጥገና አልሰጥም ማለቱን ተከትሎ ቅጣቱ ተጥሎበታል ነው የተባለው። የተባለው ችግር የተፈጠረው የኩባንያው…
Read more

የደም ምርመራና ትንተና መረጃዎችን ለመስራት የሚያስችል ሮቦት መስራታቸውን ተመራማሪዎቹ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደም ምርመራና መረጃዎቸን ትንተና ለመስራት የሚያስችል ሮቦት መስራታቸውን ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል። በሩትገርስ ዩንቨርስቲ ተመራማሪዎች የተሰራው አዲሱ ሮቦት ትክክለኛና ወቅታዊ የደም ምርመራ ውጤትና ትንተና መረጃ በመስጠት የዘርፉን ባለሙያዎችና ህሙማን ያግዛል ተብሏል። ቴክኖሎጂው በተገጠመለት ካሜራ የሰዎቹን እጅ ስካን በማድረግ በቀላሉ የደም ስሮችን በመለየት ቀደም ሲል ባለሙያዎች በመርፌ በመሰርሰር የደም ስሮችን ይፈልጉ የነበረውን…
Read more

ስፔስ ኤክስ እጅግ ትልቅ አቅም ያለው ወታደራዊ ሮኬት አመጠቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2010 (ኤፍቢሲ) በዩናይትድ ስቴትስ ስፔስ ኤክስ የተሰኘው የግል ኩባንያ በዓለም ላይ እጅግ ትልቅ አቅም ያለው ሮኬት ማምጠቁን አስታወቀ፡፡ ፋልከን ሄቪይ በመባል የሚታወቀው ይህ ሮኬት በፍሎሪዳ ግዛት በሚገኘው ከኬኔዲ የህዋ ማዕከል መነሳቱ ተነግሯል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል እንዳስታወቀው ፋልከን ወደ ህዋ የተላከው ሚስጥራዊ ለሆነ ወታደራዊ ተልእኮ መሆኑን አስታውቋል፡፡ አየር ኃይሉ አሁን ያመጠቀው ሳተላይት…
Read more

ጎግል የበይነ መረብ አገልግሎት ሳይኖር መረጃዎችን ለመጠቀም የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ18፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል የበይነ መረብ አገልግሎት ሳይኖር መረጃዎችን ለመጠቀም የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ማድረጉ ተገልጿል። መተግበሪያው የሞባይል ኔት ወርክ የማስፋፋት ውስንነት ባለባቸውና የበይነ መረብ መቆራረጥ ችግር የሚያጋጥማቸው አካባቢዎችን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።  ቴክኖሎጂው በተለያዩ አካባቢዎች ተፈላጊነት ያላቸውን አርቲክሎች እየመረጠ የበይነ መረብ አገልግሎት በማይኖርበት ጊዜ ለማንበብ እንደሚያስችል ነው የተገለጸው። ከዚህም ሌላ ደንበኞቹ ወደ…
Read more