Tag: ሌሎች ዜናዎች:

Home of best apps

ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ከመረጃ መረብ ብርበራ ጋር በተያያዘ 120 ሺህ ዩሮ ቅጣት ተወሰነበት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎቹን መረጃ ለመረጃ በርባሪዎች እንዲጋለጥ አድርጓል በሚል የ120 ሺህ ዩሮ ቅጣት ተወሰነበት። የተማሪዎቹ መረጃ በፈረንጆቹ 2004 በዩኒቨርሲቲው አንድ የትምህርት ክፍል በተዘጋጀው አነስተኛ ድረ ገጽ ላይ የተጫነ እና ለመረጃ በርባሪዎቹ መጋለጡም ነው የተገለጸው።  ይህ አነስተኛ ድረ ገጽ በወቅቱ ለሚሰጥ ስልጠና ከዩኒቨርሲቲው እውቅና ውጭ የተዘጋጀ ሲሆን፥ ተቋሙ የተማሪዎቹ መረጃ ለመረጃ…
Read more

አማዞን የሰዎችን ማንነት በፊት ብቻ መለየት የሚያስችለውን መሳሪያ ለገበያ እንዳያቀርብ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት፣ 15 2010(ኤፍቢሲ) የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሰዎችን ማንነት በፊት ብቻ መለየት የሚያስችለው መሳሪያ አማዞን ለመንግስት እና ሌሎች መሳሪያን ለሚፈልጉ አካላት ማቅረብ እንደሌለበት አሳሰቡ። ተሟጋቾቹ ይህ መሳሪያ በስደተኞች እና በቆዳ ቀለም ምክንያት ሰዎች ተፅዕኖ እንደሚደርስባቸው የሚያደርግ በመሆኑ ተግባራዊ መሆን የለበትም ብለዋል። ከ40 በላይ የሚሆኑት የመብት ተሟጋቾች ለአማዞን የኦንላይን ገበያ ስፍራ ባለቤት ለሆኑት ጆፍ ቤዞስ…
Read more

ፌስ ቡክ ከመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ለደንበኞቹ የካሳ ክፍያ እንደማይፈጽም ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት17፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስ ቡክ ካምብሪጅ አናሊይቲካ በደንበኞቹ ላይ አደረሰ ከተባለው የመረጃ ብርበራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ የካሳ ክፍያ እንደማይከፍል አስታውቋል። ኩባንያው ለደንበኞቹ የካሳ ክፍያ የማይፈጽም መሆኑን የገለጸው ከዚህ ሳምንት በፊት በብራሰልስ የአውሮፓ ህብረት ህግ አውጪዎች ለኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ማርክ ዙከርበርግ የክፍያ ከሳን በተመለከተ ላቀረቡላቸው ጥያቄ በተሰጠ የጽሁ ምላሽ ነው ተብሏል። የአውሮፓ ህብረት ህግ አውጪዎች የህብረቱ ሀገራት…
Read more

በአውሮፓ የአሜሪካ የዜና ምንጮች በአህጉሪቷ ድረገጾች ላይ እንዳይታዩ ታገዱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት የመረጃ ከለላ ህግን በስራ ላይ በማዋሉ ምክንያት ታዋቂነትን ያተረፉ የአሜሪካ የዜና ምንጮች በአህጉሪቷ ድረገጾች እንዳይታዩ ታገዱ፡፡ በአውሮፓ በሚገኙ ሀገራት ከታገዱት የዜና ምንጮች መካከል ቺካጎ ታይምስና ሎስአንጀለስ ታይምስ ይገኙበታል ተብሏል፡፡ አጠቃላይ የመረጃ ከለላ መመሪያ በሚል የወጣው ህግ ለአውሮፓውያን ዜጎች በመረጃ አጠቃቀም ዙሪያ ተጨማሪ መብት ያጎናጽፋል ተብሏል፡፡ አሁን የወጣው…
Read more

ሁለት የካናዳ ባንኮች የመረጃ መረብ በርባሪዎች ጥቃት ኢላማ ሆነዋል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ ሁለት ትልልቅ ባንኮች በመረጃ መረብ በርባሪዎች መመታታቸውን ገለጹ። በሃገሪቱ አራተኛ እና አምስተኛ የሆኑት የሞንትሪያል ባንክ እና የካናዳ ንግድ ባንኮች ወደ 90 ሺህ የሚደርሱ ደንበኞቻቸው መረጃ ሳይበረበር እንዳልቀረ ገልጸዋል። የሞንትሪያል ባንክ ካሉት 8 ሚሊየን ደንበኞች መካከል እስከ 50 ሺህ የሚደርሱት ደንበኞቹ መረጃ ሳይበረበር እንዳልቀረ አስታውቋል።…
Read more

አፕል የአይፎን ስልክን በመጠቀም ቤት እና መኪናን መቆለፍ እና መክፈት የሚያስችል አገልግሎት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት፣ 22፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ)አፕል ኤንኤፍሲ በተሰኘ ማሻሻያው ሰዎች በአይፎን ስልካቸው የቤት በሮችን፣ መኪናዎችን መክፈት እና መዝጋት የሚያስችላቸውን እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያዎችን መፈፀም የሚያስችል አገልግሎት በቅርቡ ሊጀምር ነው። ኤንኤፍሲ በተሰኘው እና በተሻሻለው የአይፎን የስልክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ስልካቸውን በመጠቀም የቤት በሮችን መክፈት እና መዝጋት፣ መኪናዎችን፣ የህናፃዎችን የደህንነት ስርዓት መቆጣጠር ይችላሉ። ከዚህ በተጨማሪ የጤና አገልግሎት እና የህዝብ…
Read more

ለአሽከርካሪዎች መረጃ የሚያቀብለው ስማርት የትራፊክ መብራት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለአሽከርካሪዎች ቀድሞ መረጃ የሚያቀብል ስማርት የትራፊክ መብራት በብሪታኒያ እየተሞከረ መሆኑ ተሰምቷል። አዲሱ ስማርት የትራፊክ መብራት አሽከርካሪዎች ቀጣይ የትራፊክ መብራት አረንጓዴ በርቶ እያለ መድረስ እንዲችሉ በምን ያክል ፍጥነት ማሽከርከር እንዳለባቸው መልእከት የሚያስተላልፍ ነው ተብሏል። ቴክኖሎጂው በኔትዎርክ አማካኝነት ለአሽከርካሪዎች መልእክቱን የሚያስተላልፍ መሆኑም ተገልጿል። ይህም ተሽከርካሪዎች የትራፊክ መብራት ላይ ቆመው የሚያባክኑትን ጊዜ…
Read more

ቀጣዩ አይፎን ስማርት ስልክ 3D ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ 3 ካሜራዎች ይኖረዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀጣዮ የፈረንጆቹ 2019 ለገበያ የሚቀርበው አዲስ የአይፎን ስማርት ስልክ 3D ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ሶስት የጀርባ ካሜራ የሚገጠምለት መሆኑ ተሰምቷል። ካሜራዎቹም ከርቀት ያለ ነገርን በማቅረብ ከፈትኛ ጥራት ፎቶ ግራፍ ማንሳትም ይሆን ቪዲዮ ለመቅረፅ የሚያስችሉ መሆኑም ታውቋል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ከሶስቱ ካሜራዎች ውስጥ ሁለቱ ካሜራዎች ምስሎችን ከተለያየ አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ማንሳት የሚያስችል…
Read more

ፌስቡክ የተጠቀሚዎችን መረጃ ለቴክኖሎጂ ቁስ አምራቾች አሳልፎ ሰጥቷል በሚል የቀረበበትን ክስ ውድቅ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃ ያለፍቃድ እና ያለአግባብ አፕልን ጨምሮ ለሌሎች የቴክኖሎጂ መገልገያ አምራች ኩባንያዎች አሳልፎ ሰጥቷል በሚል የቀረበበትን ክስ ውድቅ አደረገ። ክሱን ኒው ዮርክ ታይም ጋዜጣ ያቀረበበት ሲሆን፥ ፌስቡክ ግን በክሱ ላይ የቀረበው መረጃ እውነት አይደለም ሲል ክሱን ውድቅ አድርጎታል። ጋዜጣው ባወጣው ሪፖርት መሰረት ፌስቡክ ከ10 ዓመት በፊት ስራ…
Read more

ካርበን ዳይኦክሳይድ ጋዝን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችለውን ብረት በጥናት ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ካርበን ዳይኦክሳይድ ጋዝን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችለውን ብረት በጥናት ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ገልጸዋል። ተመራማሪዎቹ በዴላዋሬ ዩንቨርሲቲ ‘‘ቢስምዩዝ’’ በተባለው ብረት ላይ ባደረጉት ጥናት የካርበን ዳይኦክሳይድ ጋዝ መጠን ከከባቢ አየር ለመቀነስና በቀጣይነት የነዳጅ ምንጭ በመሆን ሊያገለግል እንደሚችል ማረጋገጣቸው ነው የተገለጸው። አሁን ላይ ‘‘ቢስምዩዝ’’ ለጥይት፣ ጌጣጌጥና በአሲድ የማይጠቁ ቁሳቁሶችን ለማስራት አገልግሎት ላይ እንደሚውልም ዘገባው…
Read more

ሻርፕ የተባለው የጃፓን ኩባንያ ቶሽባ ኩባንያን በ36 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሊገዛ መሆኑ ገለጸ

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 28፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጃፓኑ ሻርፕ ኮርፖሬሽን ቶሽባ ላብቶፕ ኩባንያን በ36 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሊገዛ መሆኑን አስታውቋል። ሻርፕ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ በላፕ ቶፕ ገበያ የመሳተፍ ፍላጎት ያሳየ ሲሆን፥ ካሳለፍነው የፈረንጆቹ ጥቅምት ወር ጀምሮ ከቶሽባ ላፕቶፕ ኩባንያ የ80ነጥብ1 በመቶ ድርሻ ስምምነት መውስዱ ነው የተገለጸው።  የቶሽባ የንግድ ምልክት ወደ ሻርብ ኩባንያ ከመቀየሩ በፊትም በታይዋኑ ፎክስኮን…
Read more

አፕል ኩባንያ የፌስቡክ አገልግሎትን ሊያቋርጥ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት28፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) አፕል ኩባንያ የፌስቡክ አገልግሎትን ሊያቋርጥ መሆኑ ተገልጿል። አፕል ኩባንያ የፌስቡክ ኩባንያ ወደ ፊት አገልግሎት ላይ ሊያውላቸው በሆኑት ‘‘አይኦስ’’ እና ‘‘ኤምኤሲ’’ በተባሉት  ሶፍትዌሮች  አሰራር ምክንያት የፌስቡክ አገልግሎትን ሊቋርጥ መሆኑን ገልጿል። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ደንበኞች አገልግሎት ላይ የሚያውሏቸውን የኤክትሮኒክስ መሳሪያዎችንና የሚጫኑ መረጃዎችን የሚሰጡ ናቸው ከሚል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ኩባንያው የፌስቡክ አገልግሎትን ሊያቋርጥ መሆኑን ገልጿል። የፌስቡክ…
Read more